” በድሬዳዋ አስተዳደር ከለውጡ ማግስት ወዲህ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በፖለቲካዊና በገፅታ ግንባታ ስራዎች አበረታች ውጤት የተመዘገበ ሲሆን ማህበረሰቡም ከውጤቱ ተጠቃሚ እየሆነ ይገኛል”:-የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር
በድሬዳዋ አስተዳደር ከለውጡ ማግስት ወዲህ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በፖለቲካዊና በገፅታ ግንባታ ስራዎች አበረታች ውጤት የተመዘገበ ሲሆን ማህበረሰቡም ከውጤቱ ተጠቃሚ እየሆነ እንደሚገኝ ድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ተናግረዋል። “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” ! በሚል መሪ ቃል በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተዘጋጀ የግማሽ አመት ማጠቃለያ ኮንፍረንስ እየተካሄደ ይገኛል። በዚህም በመርሃ-ግብሩ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት…


