Hojiin Babal’isa dhaabbata Simintoo Paayunar gaarii fi abdiqabeessaa jedhan
Jilli Itti-Aanaa Kantiibaa fi Hooganaan Biiroo, Daldala Indastirii fi Invastimantii Bulchiinsa Dirree Dhawaa Obbo Harbii Buuhii fi Deetaa Ministeera Inarjii Obbo Miliyoon Maatiyoosiin duurfame sadarkaa Hojiin Babal’isa dhaabbata Simintoo Paayunar irra ga’e ilaalchisuun daawwannaa taasisan irratti Obbo Miliyoon akka jedhanitti Hojiin Babal’isa dhaabbata Simintoo Paayunar gaarii fi abdiqabeessaa jedhan. Hojii gaggeessan dhaabbata Simintoo Paayunar Dr….
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች የጋራ መድረክ መካሄድ ጀመረ::
የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት እና የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ከፍተኛ አመራሮች የጋራ መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡ የጋራ መድረኩ በዛሬው ውሎው የፓርቲውን የ10 ወራት የስራ አፈፃፀም መገምገሙን ከፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ባለፉት 10 ወራት ያከናወናቸው ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በጥልቀት መገምገሙ ተመላክቷል፡፡…
በባቡር ላይ የሚስተዋሉትን ስርቆቶች ለመከላከል ያለመ ውይይት ተካሄደ።
ባቡር በሀገራችን የትራንስፖርት ዘርፍ ትልቅ አስተዋፆ እያበረከተ የሚገኝ ሲሆን በተለይም መንግስት ለዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት አዳዲስና እጅግ ዘመናዊ የሆኑ ባቡሮችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባት ለነዋሪው ህብረተሰብ አገልግሎት እንዲሰጡ ከመደረጉም በዘለለ የባቡር ጣቢያዎችን ዘመናዊ በሆነ መልኩ በማስገንባት ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ ተደርገዋል ። ባቡር ለነዋሪው ህብረተሰብ ከፍተኛ አገልግሎት እየሰጠ ቢገኝም ነገር ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በባቡር ላይ…
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የተከበሩ ሀርቢ ቡህ ለኢድ አል ፈጥር በዓል ያስተላለፉት መልዕክት…….!!
ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ 1 ሺህ 445ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዳን ወር ጾም ፍቺ፣ ዒድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል። ህዝበ ሙስሊሙ ባለፉት 30 ቀናት በጾምና ጸሎት ማሳለፉን በመጥቀስ የረመዳን ወር ከፈጣሪ ምህረት የሚለመንበት፣ መረዳዳት የሚጠናከርበትና በጎ ተግባራት የሚስፋፋበት ወር በመሆኑ የኢድ በዓልም የደስታ፣ የእዝነትና የርህራሄ የመተሳሰብ፣ ያለው ለሌው በማካፈል በአብሮነት የምናሳልፈው ማህበራዊ ግንኙነትን…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሴራሊዮን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጁሊየስ ማዳ ባዮን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ጁሊየስ ማዳ ባዮን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን በማሕበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሑፍ አስታውቀዋል።
በኢትዮጵያ የብስክሌት ስፖርት ውድድር ታሪክ ውስጥ በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የጥሎ ማለፍ የታዳጊዎች ውድድር በድሬዳዋ ተከናወነ
የፈናን ፔይ የብስክሌት ሻምፒዮና የጥሎ ማለፍ ጫወታ አንደኛና ሁለተኛ ሆነው ባጠናቀቁት በአቤኔዘር አለሙና እና ኢሳኮር ፍሬው መካከል የታየው ፉክክር በስፍራው ከታደመው የስፖርት አፍቃሪ እና ተመልካች ከፍተኛ አድናቆት ተችሮታል። አርባ ሁለት ዙሮችን በሚሸፍነውና በያንዳንዱ ዙር መጨረሻ የሆነ ተወዳዳሪ ከጫወታ ውጪ እየሆነ የመጨረሻዎቹ ሁለት ተወዳዳሪዎች እስኪቀሩ ድረስ ጠንካራ ፣ አጓጊና ብርቱ ፉክክር በታየበት በዚህ በአራተኛው ቀን የፈናን…
የድሬደዋ ደወሌ ምድር ባቡር ያለዉን እምቅ ሀብት በመጠቀም ለከተማዋ ብሎም ለምስራቅ ኢትዮጲያ ኩራት የሆነ ተቋም ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።
በአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የተመራ ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ አመራሮች የድሬደዋ ደወሌ ምድር ባቡርን ጎብኝተዋል።በቅርቡ የሚኒስትሮች ም/ቤት መጋቢት 24 ቀን 2014 ባሣለፈዉ ዉሣኔ የድሬደዋ አስተዳደር ከድሬደዋ እስከ ደወሌ ድረስ ያለዉን የምድር ባቡር ንብረት በባለቤትነት እንዲያስተዳድር መወሠኑ የሚታወስ ነዉ።በጉብኝቱ ላይ የአስተዳደሩ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊን ጨምሮ የንብረት ርክክብ ኮሚቴ አባላትና የተለያዩ አመራሮች ተገኝተዋል። ዘገባው…
ዜና/”የህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያዉያንን በአንድ አስተሳስሮ ወደ ልማት ያስገባና ወሳኝ የኢኮኖሚ ሴንተር እንቅስቃሴ መሆኑ በተፋጠነ ርብርብ አጠናቆ በሙሉ አቅሙ ስራ እንዲጀምር ርብርብ ማድረግ ይገባል”
DGC መጋቢት 26/2017 “ኢትዮጵያ ትችላለች” በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከድሬዳዋ አስተዳደር የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን 14ኛ አመት በዓል የሚዘክር የውይይት መድረክ አካሄደ። በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ይህ ቀን የሚከበረው ሀገራችን ኢትዮጲያ በመጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም ለተበሰረው…
“በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በአንድ መንፈስ በመላው ኢትዮጵያ ዓሻራችንን እናኑር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንድ ከሆን ከዚህም በላይ እንችላለን! ሲሉ ገልፀዋል። አዋቂዎች ከ20 በላይ፣ ታዳጊዎች ከ10 በላይ ችግኞችን በመትከል ለሀገር ያለንን ፍቅር፣ ለትውልድ ያለንን ስጦታ በተገቢው ስፍራ እንግለጥ ሲሉ…


